ረቡዕ 11 ሜይ 2016

እውነት ይህስ ትክክል ነውን ?



እውነት ይህስ ትክክል ነውን ?

እኛ ባለንበት ባሁኑ ዘመን ማስታወቂያ ዋጋ ቢስ ሲሆን ይታያል። የማስታወቂያ አላማውና ይዘቱ ሳይገባቸው ብዙ ሰዋች ማስታወቂያ ሲያስነግሩ ይታያል ማስታወቂያ እምቅ የሆነ የሰውን ልጅ የመግዛት ሃሳብን የመቆጣጠር ደስ የማሰኘት የማስከፋት ትልቅ ችሎታ ያለው አንዱ ማስታወቂያ ነው።
     ታዲያ ከሰሞኑ ኢ.ቢ.ሲ ሲተላለፍ ያየሁት የፍራሽ ማስታወቂያ እጅግ የሚገርም እና በስህተቶች የተሞላ ነበር ፤በዚህ የፍራሽ ማስታወቂያ ላይ ብዙ አርቲስቶች የተሳተፉ ሲሆን ስለፍራሽ ለማስተዋወቅ የተጠቀሙት የመረጡት ቃል በጣም ግነት የበዛበት እና የሌላውን ምርት የሚያንቋሽሽ ነበር። (በዚህ ፍራሽ ሃሳቦን ጥለው ለሽ)
ፍራሹን ሲያስተዋውቁ ሁለተ ሰዎችን እያነፃፀሩ አንዱ የተኛበት ፍራሽ የሌላ ምርት ስለነበረ ቢሮውስጥ ሲገባ ወገቡን ታሞ እና እንቅልፉን እያንቀላፋ ነበር። የገረመኝ ነገር ይህ ነበር የነሱን ፍራሽ ላይ ተኝታ ያደረችው አርቲስት ደግሞ በጠዋቱ ተነስታ ደስ ብሏት ሳቅ ሳቅ እያላት እየጨፈረች ነበር። ከዚያም በስጦታ መልክ አስመስላ ለሱ ፍራሹን እንዲገዛ እና እንዲጠቀም ካደረገችው በኋላ የተሳካለተ እንቅልፍ ተኝቶ ለሌላ ሰወ ሲናገር ይታያል። ታዲያ ይህ በትልቅ ግነት የተሞላ ፍራሽ ማስታወቂያ ማስተዋወቅ ካለባቸው ያንዱን እያጥላሉ ሳይሆን የራሳቸውን ምርት ለየት ያለ ነገር በመጠቀም መሆን ነበረበት። ይህ አይነት ተግባር ተገቢ ያልሆነ እና በህግም ሊያስቀጣ ይችላል።

ሌላኛው ደግሞ በዚህ ፍራሽ ማስታወቂያ ላይ ያየሁት አንድ ነገር ይህ በጣም የተጋነነ እና የማይመስል ነገር ነው። ፍራሹ ላየ ሰውዬው ከተኛ በኋላ ለሊቱም አልፎ ጠዋትም ሳይነሳ ቀርቶ ሰዎች ቀስቅሰውት ተመልሶ የመተኛት ሁኔታ ይታይበት ነበር። እና እንዲህ አይነቱ የማስታወቂያ አይነት ማስተላለፍ ከፈለገው መልዕክት የወጣ ይሆናል። ለምሳሌ፡- ለስራው እንቅፋት መሆንና በጠዋት አለመነሳትን ጥሩ ያልሆነ ጎኑን ያሳያል። ከዚህም በተጨማሪ የፍራሹ ላይ ተኝታ ስትነሳ ጥሩ ቁርስ በልታ ቀኑን ሙሉ ደስተኛ ስትሆን ይታያል ነገር ግን ሌላኛው ደግሞ ቁርሱንም ቢበላ በፍራሹ ምክንያት ደስተኛ ሳይሆን መቅረቱን ያመላክት ነበር። ይህ ማለት ደግሞ ከነሱ ፍራሽ ላይ ያልተኛ ሰው ጥሩ ቁርስ ቢበላ ደስተኛ አይሆንም ለማለት የፈለጉ ይመስላል።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ