ማክሰኞ 17 ሜይ 2016

ከመሞት መሠንበት


                           ከመሞት መሠንበት


ማስታወቂያ የተጀመረው በአንሽንት ባቢሎኒያን የመጀመሪያ ማስታወቂያ የተሠራው በእንግሊዝኛ ነዉ፡፡እናምማስታወቂያወች እንደምናውቀው በድሮ ዘመን ነው አባቶቻችንን ማስታወቂያ በፈለጉት መልኩ  የተሠማቸዉን ነገር በቅርፃቅርፃ መልኩ በግድግዳ ላይ ሠረተዉ አልፈው ነበር እናም ዛሬእኛ ይህንን ተግባር ከአባቶች ተቀብለን ይዘን እናስቀጥላለን ነገር ግን የተለያዬ ድክመቶች በዉስጡ ይዙ ይገኛል ይህም ያልኩበት ምክኒያት አሁን እኛ ባለንበት ዘመን ማስታወቂያወች እየተገለባበጡ ለሠወች ግልፅ ባልሆነ መልኩ ማለትም ያልተማርዉን ማህበረሠብ በመርሳት ዘመኑ ባመጣቸው ቆንቆወች በመተካት ሠወች ሊያዬቸዉ እንጂ ሊገባቸው በማይችልበት መልኩ መሠራት ጀምረዋል የዚሕም ምክኒያቱ እኛ ለራሣችን ያለን አመለካከት መዉረድና በሌሉች እራሣችንን ጥገኛ አርገን መመልከታችን በቡልጭልጭ ነገር መታለላችንና አለማወቃችን ነዉ፡፡

ማስታወቂያ  በአሁ ዘመን ከመሞት መሠንበት በሆነበት ዘመን እስኪ በአሁኑ ዘመን በአካባቢያችን ያሉ ባነሮች,ቢልቦርዶች እንመልከት በተለያዩ ቋንቋዎች የተሞሉ ማስታወቂያዉን በማይገልጽ ንግግር የያዘ ነዉ ይህ ደግሞ የሆነበትን ስንመለከት ቋንቋወች ወደ ዉጭ ሀገር ቋንቋዎች እየተቀየሩ እናአማርኛ እየጠፋ ያለበት ሁኔታ እንመለከታለን ይህ የሆነው ሠዎች ሰልጣኔ ብለዉ ያመጡት ያልሆነ እና ተገቢ ያላደለ ነገር ነዉ፡፡ ምን አልባት በኢትዮጵያ ከ100/15ፐርሠንት ብቻሊሆን ይችላል የዉጭ ሀገር ቋንቋ የሚናገር ሠዉ  ሌላኛውን ደግሞ ስንመለከት የራሡን ቆንቆ ብቻ የሚናገር ነዉ ነገር ግን ህዝቡ ይህንን ግምት ውስጥ ሳያስገባ በግዛዊ ነገር ተታሎ የራሡን ቋንቋ በደንብ ማስፋፋት እና ማቅረብ እየቻለ ባለማወቁ ምክኒያት የሌላ ቋንቋ ተገዥ እየሆነ የመጣበት ሁኔታ እንመለከታለን ታዲያ ይህ አሣሣቢ እና ከግዜ ወደ
ግዜ እየተባባሠ መጥቷል፡፡

በስልጣኔ ምክኒያት ነዉ እያልን ያመጣነዉ ነገር ሣናዉቅም ሆነ እያወቅነ የኛን ቋንቋ እየገደለብንና የሌላ ቋንቋ ተገዥ እያደረገን ነዉ አንድ ያላወቅነው ነገረ ቢኖር የራሣችንን ቋንቋ ንቀን የሠው ቋንቋ በመከተል እራሣችንን ዝቅ እያደረግነው የመጣነዉ .ስለዚህ ማስታወቂያወች በእንግሊዘኛ የሚሠራበት ዋነኛ ምክኒያት ህዝቡ ስለ ራሡ ማንነት በቂ እውቀትና ግንዛቤ ስለጎደለው ይህ ዋነኛ ምክኒያቱ ሲሆን ሰልጣኔ ብለን ያመጣነዉ ነገረ ሁለተኛ ምክንያት ነወ የመንግስት ጥብቅ ክትትል በማስታወቂያ ዙሬያ ስለማይደረግ ነዉወይም ለቋንቋ ግዴለሽ በመሆን ምክኒያት የመጣ ነዉ፡፡




ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ