ረቡዕ 11 ሜይ 2016



                                                   ሳይበሉ የወዙ
ብዙ ማስታወቂያዎች ፆታዊ አድሎ የበዛባቸው እና የሴት የወንድ እየተባለ እየተከፋፈለ የመጣበት ሁኔታ ይታያል። ሰዎች በተለምዶ ሰዎች በተለምዶ ሴት ወንድ ሽማግሌ ወጣት እያሉ እንደየድርሻው የማይሆን ቦታ ላይ ይከፋፍሏቸዋል። ብዙ ማስታወቂያዎች ስንመለከት እነዚህ የተዘረዘሩ ነገሮች አሉባቸው። ለምሳሌ ሴትን ፀሀፊ የማድረግ ወንድን የቢሮ አዛዠ አለቃ እያደረጉ ለብዙ ጊዜ ማስታወቂያ በመስራት ኖረዋል።  
የቫዝሊን ሎሽን ማስታወቂያ ስንመለከት ብዙ ጊዜ ሴቶች ናቸው ተጠቃሚ በሚል ሀሳብ ማስታወቂያውን የሚያሰሩት በሴት እህቶቻችን ነው።  በማህበረሰቡ ዘንድም እንደዚህ አይነት አመለካከተ ስላለ ሴቶች ሎሽን ላይ ቅባት ላይ ማስታወቂያ እድዲሰሩ ያደርጋሉ ይህ ደግሞ ሴትነትን ለሌላ ነገር እንደመጠቀም ማለት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የዚህን የሎሽን ማስታወቂያ  ስንመለከት ከወገቧ በላይ እራቁቷን የሆነች ሴት ነው የሚያሰሳየን።
ይህ ተገቢ ያልሆነ የማስታወቂያ ስራ ሴቶች ተገላልጠው ወንዶችን ለማማለል። የተጠቀሙበት ነገር ይመስላል።
በዚህ የቫዝሊን ማስታወቂያ ያየሁት ጉድለት ቫዝሊኑን የተቀባች ሴት ጠረኗ ከሩቅ እደሚስብ እና ሰዎች መንገዳቸውን እየሳቱ ወደሷ የሚሄዱበት አጋጣሚ ተከስቶ ነበር። ያቀፋትም ወንድ በጠረኗ ተማርኮ ብዙ ጊዜ አንገቷ ላይ ጥምጥም በማለት አለቃት እንዳለ እና እሱም ሄዶ ያንን ሎሽን መጠቀም እንደጀመረ ይገልፃል። ይህ ከፍተኛ ግነት ያለበት ማስታወቂያ ነው። ምክንያቱም  ያንን ሎሽን የተቀባች ሴት ወንዶች ይወዷታ እያሉን ነው ማለት ነው።

ሌላኛወ ስህተት ደግሞ የተመላለጠ እና የተበላሸ ቆዳ አምጥተው የዛን ሎሽን ተጠቃሚ ከሆነች በኋላ ቆዳዋ ሲመለስ ያመላክታል። ይህ ትልቅ ውሸት ነው። ማስታወቂያውን የሚሰሩት ሰዎች ብዙውን ጊዜ የውጭ ሃገር ሰዎች ናቸው።    ስለዚህ ማስታወቂያው መሰራት የነበረበት በሀገር ውስጥ የማስታወቂያ ሰሪዎች መሆን ሲገባ በውጭ ሀገር ሰዎች መሰራት አልነበረበትም። እደባህላችንም መገላለጥ ከባህላችን ጋር የሚፃረር ነገር ሲያደርጉ ይስተዋላሉ። ይህ ማስታወቂያ ባጠቃላይ ግነትን ከባህል አንፃር ከፆታም አኳያ እንከን የበዛበት ማስታወቂያ ነው።


                         

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ