ሳይቃጠል በቅጠል!
ማስታወቂያ የህብረተሰብን ምርትን ወይም አገልግሎትን
አሰጣጥን የሽያጭ እንቅስቃሴዎች ላይ ተፅህኖ በማሳደር ለሃደሪቱ እድገት ከፍተኛ ሚና የሚጫወተ ነው። ይህ መሆን የሚችለው ግን ማስታወቂያ
ስርሃት ባለው መልኩ ሲተለላለፍ እና የህብረተሰቡን ባህል እና ወግ መብት እና ጥቅም ጠብቆ ሲቀርብ ብቻ ነው።
በኢትዮዺያ በርካታ የማስታወቂያ ስራ
የሚሰራ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም የተነሳ ብዙ ማስታወቂያዎች ይዘት እና መልካቸውን ቀይረው ወዳልሆነ መንገድ ሲመሩን ወይም ሲጓዙ
ይስተዋላል።
ለምሳሌ፡-
የኮካ-ኮላ ማስታወቂያ ብንመለከት በኢ.ቢ.ሲም ሆነ በቢልቦርድ ላይ የተመለከተው ሰው ብዙ እንከኖች ያሉበት እና ግነት የተሞላበት
ነው። ይህን ማስታወቂያ ስንመለከት የኛን ባህል ወግ ልምድ የቃላት አጠቃቀም ምንም የማይገልፅ ነው።
ከባህል አንፃር ስናየው ማስታወቂያው
የሚሰራው ለኢትዮዸያውያን ሆኖ ነገር ግን ማስታወቂያው በውጭ ሀገር ማስታወቂያ ሰሪዎች የተሰራ ነው። የማጀቢያውን ሙዚቃውን ስንመለከት
እግሊዘኛ ሙዚቃ ነው። ይህ ደግሞ ባህላችን በማንነታችን ኦለመኩራታችንን ያመላክታል። ሰዎች የራሳቸውን ባህል እና ወግ ልምድ ትተው
ወደ ውጭ ሃገር በመሳብ ምርት እና አገልግሎትን በባዕድ አገር ቋንቋ በተበረዘ መልኩ ማስታወቂያውን ሲያስተላልፉ እንመለከታለን።
ይህ አይነቱ ስራ ተገቢ ያልሆነ ነገር ነው። የስራ ቋንቋችን አማረኛ እንደመሆኑ መጠን መጠቀም ያለብን በራሳችን ቋንቋ ነው።
በዚህ
የኮካ ኮላ ማስታወቂያ ላይ ያልተገባ የአስማት ስራ የተካተተበት እና ሰዎች ወደመጥፎ የሚመራ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎች ማስታወቂያውን
የገለፁበት መንገድ ያለምንም ንግግር ስለነበር ማንኛውም ሰው እደየራሱ አመለካከት ሊተረጉመው ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ በምስል
ብቻ አይተው ሊረዱ አይችሉም ስለዚህ ማስታወቂያ ሙሉ መሆን እና ምን ማስተላለፍ እንደተፈለገ በግልፅ መቀመጥ መቻልአለበት።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ