ሳናውቅ ያወቅነው
ማስስታወቂያ
በባህሪው አላማው ምርት እና አገልግሎትን ለሰዎች ግልፅ እና ቀላል በሆነ ቋንቋ ሰዎች በቀላሉ እንዲረዱ ማድረግ ሲሆን ማስታወቂያ
ግቡን ሊመታ የሚችለው ተጠቃሚውን እና አገልግሎተ ሰጪውን ሊያግባባ በሚችል ቋንቋ ቦታ እና ጊዜ የቀረበ ከሆነ ነው። ወደ ሰሜናዊት
ኮከብ መቐለ ስንመጣ ብዙ ማስታወቂያዎችን ተመልክቼ ነበር። ነገር ግን ማስታወቂያዎችን በቢል ቦርድ በባነር በፖስተር የተዋቀሩ ናቸው
እነዚህ ማስታወቂያዎች ላይ ያልተገባ ቃላት እና ስህተቶችን ተመልክቻለው።
ለምሳሌ
ባቅራቢያችን ባለው (ኬር ጁስ ቤት) ብንመለከት ሲጀምር ከስር መሰረቱ ባነሩ ላይ የተፃፈወ ፅሁፍ (ኬር ጁስ ሃውስ) ነው የሚለው።
ይህ ደግሞ ኬር ጁስ ቤት የሚለውን አይወክልም ምክንያቱም በማስታወቂያ ህግ አንድ ማስታወቂያ በአማረኛ በእግሊዘኛ ተቀላቅለው መፃፍ
የለበትም ወይንም በእንግሊዘኛ የተፃፈውን ሙሉ በሙሉ ወደ አማረኛ በመተርጎም ያልተቀየጠ ቋንቋ መፍጠር ይቻላል። ምክንያቱም በመቐለ
እና አካባቢዋ የስራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ ሰለሆነ ማንኛውም ማስታውቅያ ለህብረተስቡ ግልፅና ቀላል በሆነ ቋንቋ መተላለፍ አለበት።
በዚህ
ዘመን ዘመናዊነት እያልን ያመጣነው
አዲስ
ነገር የኛን ባህል የሚጎዳ ነው። ሌላኛው ደግሞ ከዛ ባነር ላይ የሉት
የቀለም መብዛትና ፊደላት ከቀለሙ ጋር ያለመጣጣመ ሁኔታ ይታይባቸዋል
ይህን ስንል እያንደንዱ ፅሁፍ በተላያየ የቀለም አይነት ነው የተፃፈው።
ከዛም የባነሩ ቀለም ደማቅ እና ቅዠርዠር ያለ ነው። የቋንቋም አጠቃቀሙም
ላይ አማረኛ እና እንግሊዘኛ ስለሆነ ከህጉ አንፃር ስንሄድ የማይፈቀድ ተግባር ነው። በባነሩ ላይ ያሉት ስህሎችም ጥራታቸውን የቃልጠበቁ
እና ጎላ ብለው የማይታዩ ናቸው። እንዲሁም ጁስ ቤት ከመሆኑ አንፃር ብዙ ፍራፍሬ ሳይሆን የጁስ ምስሎች መቀመጥ መቻል ነበረባቸው።
ነገር ግን ሰው ፍራፍሬ ቤት እስኪመስለው ድረስ በፍራፍሬ ስዕል የተሞላ እና የጁሶቹ ምስል በፍፋፍፌው ተሸፍኗል። ይህ ደግሞ ሰው
ፍራፍሬ ቤት ነው ሊል ይችላል። ስለዚህ ማስታወቂያ ላይ ትኩኩረታችን መሆን ያለበት ከምንፈልገው ወይንም ድርጅታችን ከሚሸጠው ላይ
ነው።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ