ሰኞ 16 ሜይ 2016


                                         እሳት ኣመድ ወለደ


የማስታወቂያ አላማው ምርትንና አገልግሎትን ማስተዋወቅ ለተጠቃሚወች ሰለ ሚሠጡት ምርት ወይም አገልግሎት መረጃ ማቅረብ ነዉ፡፡የማስታወቂያ አላማዉግቡን ሊመታ የሚችለዉ ተጠቃሚውንና አገልግሎት ሠጭዉን ሊያግባባ በሚችልቋንቋ,ቦታና ግዜ የቀረበ ከሆነብቻ ነው፡፡በዚህ መሠረት ወደ ባነር ማሰስታወቂያ ሰንመጣ አብዛኞቹ  የቋንቋ አጠቃቀማቸዉ ላይ ህግናስርአት የላቸውም ማስታወቂያ አሰነጋሬው በገባዉ በተረዳዉ መልኩየድርጅቱን ሰም ይሠይማል፡፡ሠወች ምን ያህል ሊረዱትና ሊሊገነዘበዉ ይችላል የሚል ግንዛቤ የላቸዉምቀ፡፡ለምሣሌ ራህዋ ጁስ ቤትን እንመልከት.

ራህዋ ጁስ ሀዉስ እና ካፌ ይላል ከነስር መሠረቱ ይህ የባነሩ ማስታወቂያ መቸም ዠም ብሉ ላየዉ ሠዉ መጀመሬያ ገና እንዳየዉ የፍራፍሬ መሸጫ ነዉ የሚመስለው ከዛም አስተዉለዉ ሲያዬት ቡዙ እንከኖች ያሉበት የባነር ማስታወቂያ ነዉ፡፡ ገና ባነሩን ስንመለከተዉ የተለያዩ ፍራፍሬወች ነዉ ያሉበት ያነ ደግሞ የሚያመላክተዉ ቤቱ የፍራፍሬ  መሸጫ ነዉ እንጅ የጭማቂ መሸጫ ነዉ ለማለት ይከብዳል፤፤
ከዛም በተጨማሬም ራህዋ የሚለዉ አማረኛ ሆኖ ጁስ እና ሀዉስ የሚለው ጭማቂ ቤት መባል ነበረበት፡፡ታዲያ እንዲህ አይነቱ በስህተት የተሞላ ማስታወቂያ ሀገራችን ላይ እየተበራከ መጥቶል ከስርመሠረቱምን ሲባል አማረኛን ትቶ ወደ ሌላ ቆንቆ ይጠቀማል ወይም እንግሊዘኛ ከሆነ ሁሉም እግሊዘኛ መሆን መቻል አለበት ወይም አማረኛም ከሆነ እንደዛዉ በአማረኛ መጨረስ አለበት አለበለዚያ ግን ይሕ በዉነቱ ትዉልድን የሚገድል ስራ ነዉ፡፡እንዲህ አይነቱ ማስታወቂያ ይህ ብቻ አይደለም ጉዳቱ ነገም ከነገም ወዴያ ሌላ ሠወች ስም ይወጣ ከቤት ይቀበል ጉረቤትነዉና ነገሩ ማስታወቂያዉን ሲያሠሩ ካለማወቅ የተነሣ በዛ መልኩ ሊያሠሩ ይችላሉ .ነገር ግን እንደዛ ማድረግ ተገቢ ያልሆነና አንዱ አደረገ ብለን እኛም ማድረግ የለብንም ሌላው ገደል ሲገባ አብረን መግባት የለብንምና ይህን ያልኩበት ምክኒያት ከጎኑም ያለዉ ሠመሀል ጁስ ሀዉስ ሰለሚል ነዉእናም ምክኒያታቸዉን ስጠይቃቸዉ የሠጡኝ ምላሽ ያዉ ቡዙ ቦታ ላይ እንደዛ ነዉ የሚባለዉ እናም ዘመናዊነት ነዉ ቡለዉኚ ነበር፡፡

ይህ ዘመናዊ ሆን እያልን የምናመጣዉ ማስታወቂያ ቋንቋችን በመግደልና እንደ ግዕዝ ፊደላት እንዲጠፉ የሚያደርግ ስረዓት አልባ ማስታወቂያ ነዉ፡አንድ ነገር ስንከፍት ደግሞ ስለዛ ቤት እና ስላለው ነገር ስለሚሠራበት ስራ የሚገለፅ በቂ ስዕል ና በቂ መረጃ ባነሩ ላይ ሊኖረው ይገባ ነበር.ነገር ግን ይህ ማስታወቂያ ራህዋ ጁስ ሀዉስ ና ካፌ ብሉ ስለ ካፌ አገለግሎት የሚገልፅ አንድም ነገር የለም ። ስለዚህ ኣስቀድመው ማሰብና ምን መክፈት እንደፈለጉ ምን ምስል ማስቀመጥ እንዳለባቸው ያልተገነዘቡ ይመስለኛል ። ስለዚህ በኔ ኣመለካከት ነገሮችን ያሙላ ባነር ኣይደለም 

ማስታወቂያ ማለት እኮ ለሰዎች ቅድመ ግንዛቤ መፍጠር ማለት ነው ። ነገር ግን ይህ ባነር በቂ ግንዛቤ  መፍጠር የማይችል እና ምሉ ያልሆነ ባነር ነው ። ሰዎች ማስታወቂያ ከመስራታቸው በፊት ስለ ማስታወቂያ ቅድመ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል ።ለማን ነው  ማስታወቂያው የምንሰራው ? የት ቦታ ነው ምናስቀምጠው ፣ ምን ኣይነት ቃላት ነው ምንጠቀመው ፣የኛን ባህል ይገልፅልናል ወይ ማ ለትይገባነል፤፤፤፤

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ