ረቡዕ 11 ሜይ 2016

 ስህተቱ የማነው
ብዙ ጊዜ እኛ ሰዎች ማስታወቅያን የምናስብበት ወይም የምንመለከትበት አቅጣጫ እነሱ ካሰቡት ወጣ ያለ ይሆናል ይህ የሆነበት ምክንያት ብዙን ጊዜ ማስታወቂያ የሚሰራበት ወይም በተደጋጋሚ ማስታወቂያ የሚያስነግር አንድ ምርት ገዢ አቶ ነው። ሊከስርበት ሆኖ ነው እንጂ ሌሎችማ በደንብ ተጠቃሚ ስላላቸው ማስታወቂያ አያሰሩም ብለን እናምናባለን። ነገር ግን ማስታወቂያ የአንድ ድርጅት ምርት ገፅታ ግንባታ ነው። ብዙ ገቢ የሚያሰባስብበት አንዱ ዘዴ ማስታወቂያ ነው።
ሰዎች ጥሩ እቃ ማስታወቂያ አያስፈልገውም ብለው ያምናሉ። ነገር ግን ይህ መሆን የለበትም ማስታወቂያ ጥሩ ገፅታን ለመገንባት እንጂ እቃው ዝቅተኛ ጥራት ኖሮት አይደለም።
ሰሞኑን በኢ.ቢ.ሲ ብዙ የቢራ መጠጦች ይተዋወቁ ነበር። ማስታወቂያውን በተመለከትኩ ሰዓት አንድ የቢራ ማስታወቂያ ትኩረት ሰጥቼ እየተከታተልኩት ነበር። በዚ የቢራ ማስታወቂያ ላይ ግነት ይታይበት ነበር። ማስታወቂያው ጥራት እና ይዘቱን ጠብቆ ማስተዋወቅ ሲገባን የማስተዋወቂያውን የማጀቢያ ሙዚቃ የእግሊዘኛ እና ምንም በማይታመን ሁኔታ ጠርሙሶቹ እጅ እግር ኖሯቸው የተለያዩ የዳንስ ትርዒት ሲያሳዩ ተመልክቼ ነበር። ይህ መሆኑ ደግሞ ሰዎችን ከማሳቅ እና ከማዝናናት ያለፈ ሰዎች ለምርቱ ትኩረት ሰተው ላይከታተሉት ይችላሉ። ስለዚህ እደዚ አይነቱ ማስታወቂያ ተገቢ አይደለም።

በዚህ ማስታወቂያ ላይ ሌላኛው የተመለከትኩት ነገር ቢራውን የሚጠጣው ልጅ ቢራውን በሚጠጣበት ሰዓት ከጉሮሮው ያልሆነ ድምፅ ይወጣ ነበር። እናም ቢራውን እየጠጣ የተለያዩ ሴቶች ወደሱ ሲቀርቡ እና አብረው ሲጠጡ ተመልክቼ ነበር። ይህ ማስታወቂያ ሴቶችን በቀላሉ ተላላ እና እርካሽ እቃ አድርጎ ያሳይ ነበር። ይህ ማለት እንግዲ ቢራን የሚጠጣን ወንድ ብዙ ሴቶች ይፈልጉታል እደማለት ነው።

ይህ ብዙ ተመልካች እና አድናቂ ባለው የኢ.ቢ.ሲ ፕሮግራም የሚቀርብ የቢራ ማስታወቂያ የህብረተሰብን ህልውናንም የሚነካ ተገቢ ያልሆነ ማንኛውም ማስታወቂያ የሰውን ልጅን ስብዕና ስነ ምግባር የሚፃረር የሌሎችን እምነት የሚያንቋሽሽ መሆን የለበትም። ስለዚ ይህ የቢራ ማስታወቂያ ተገቢ አይደለም።  

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ